Micah 1

1በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፤

2እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ሁላችሁም ስሙ፤
ምድር ሆይ፤ በውስጧም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፤
ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣
ልዑል እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይመሰክርባችኋል።

በሰማርያና በኢየሩሳሌም ላይ የተላለፈ ፍርድ

3እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያ ስፍራው ይመጣል፤
ወርዶም በምድር ከፍታዎች ላይ ይራመዳል።
4ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ፤
ሸለቆዎችም ይሰነጠቃሉ፤
በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፣
በገደል ላይ እንደሚወርድ ፈሳሽ ይሆናሉ።
5ይህ ሁሉ የሚሆነው ስለ ያዕቆብ በደል፣
ስለ እስራኤልም ቤት ኀጢአት ነው።
የያዕቆብ በደል ምንድን ነው?
ሰማርያ አይደለችምን?
የይሁዳስ የኰረብታ መስገጃ ምንድን ነው?
ኢየሩሳሌም አይደለችምን?

6“ስለዚህ ሰማርያን የፍርስራሽ ክምር፣
ወይን የሚተከልባትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤
ድንጋዮቿን ወደ ሸለቆ አወርዳለሁ፤
መሠረቷንም ባዶ አደርጋለሁ።
7ጣዖቶቿ ሁሉ ይሰባበራሉ፤
ለቤተ መቅደሷ የቀረበው ገጸ በረከት በእሳት ይቃጠላል፤
ምስሎቿን ሁሉ እደመስሳለሁ፤
ገጸ በረከቷን በዝሙት ዐዳሪነት እንደ ሰበሰበች ሁሉ፣
አሁንም ገጸ በረከቷ የዝሙት ዐዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል።”

ልቅሶና ሐዘን

8በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤
ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤
እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤
እንደ ጕጕትም አቃስታለሁ።
9ቍስሏ የማይሽር ነውና፤
ለይሁዳ ተርፏል፤
እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣
እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሷል።
10በጌት
ጌት የሚለው ቃል በዕብራይስጡ አውራ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው።
አታውሩት፤
ከቶም አታልቅሱ
ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ሲስማማ፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን በአኮ ላይ አታልቅሱ ይላል። በአኮ የሚለው የዕብራይስጡ ቃል አለቀሰ ከሚለው የዕብራይስጡ ቃል ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው።

በቤትዓፍራ
ቤትዓፍራ ትርጕሙ የትቢያ ቤት ማለት ነው።

በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።
11እናንት በሻፊር
ሻፊር ትርጕሙ አስደሳች ማለት ነው።
የምትኖሩ፣
ዕርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ዕለፉ፤
በጸዓናን
ጸዓናን የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ውጣ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው።
የሚኖሩ
ከዚያ አይወጡም፤
ቤትዔጼል በሐዘን ላይ ናት፤
ለእናንተም መጠጊያ ልትሆን አትችልም።
12ከመከራው መገላገልን በመሻት፣
በማሮት
ማሮት የሚለው ቃል በዕብራይስጡ መራራ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው።
የሚኖሩ በሥቃይ
ይወራጫሉ፤
እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር፣
ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷልና።
13እናንት በለኪሶ
ለኪሶ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ቡድን ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው።
የምትኖሩ፣
ፈረሶችን ከሠረገላው ጋር አያይዙ፤
ለጽዮን ሴት ልጅ፣
የኀጢአት መጀመሪያ እናንት ነበራችሁ፤
የእስራኤል በደል
በእናንተ ዘንድ ተገኝቷልና።
14ስለዚህ እናንተ ለሞሬሼትጌት፣
ማጫ ትሰጣላችሁ፤
የአክዚብ
አክዚብ ትርጕሙ አታላይ ወይም ማታለል ማለት ነው።
ከተማ፣
ለእስራኤል ነገሥታት መታለያ ትሆናለች።
15እናንት በመሪሳ
መሪሳ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ድል አድራጊ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው።
የምትኖሩ
ድል አድራጊ አመጣባችኋለሁ፤
ያ የእስራኤል ክብር የሆነው
ወደ ዓዶላም ይመጣል።
16ደስ ለምትሰኙባቸው ልጆቻችሁ፣
በሐዘን ራሳችሁን ተላጩ፤
ራሳችሁን እንደ አሞራ ራስ ተመለጡት፤
ከእናንተ በምርኮ ይወሰዳሉና።
Copyright information for AmhNASV